ኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪካን በኤሌክትሪክ መሠረት ልማት የማገናኘት ጥረቶችን እያስፋፋች መሆኑን አስታወቀች
14:57 01.06.2025 (የተሻሻለ: 15:44 01.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪካን በኤሌክትሪክ መሠረት ልማት የማገናኘት ጥረቶችን እያስፋፋች መሆኑን አስታወቀች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪካን በኤሌክትሪክ መሠረት ልማት የማገናኘት ጥረቶችን እያስፋፋች መሆኑን አስታወቀች
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ ጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳንና ኬንያን ጨምሮ ሀገራት ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት ፍላጎት አያሳዩ እንደሆነ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል። ለኃይል ጥያቄዎች በጥናት ላይ የተመሠረተ ምላሽ ለመስጠት እየተሠራ ነው ብለዋል።
ሀገሪቱ በቀጣይ እስከ ደቡብ አፍሪካ ኃይል ለማቅረብና አህጉራዊ ትስስርን ለማጠናከር ትሠራለች ሲሉም ለሚዲያው ገልፀዋል።
ከኃይል ሽያጭ የምታገኘው ገቢ እያደገ መሆኑንና በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ብቻ ለጎረቤት ሀገራት እና ለክሪፕቶ ማይኒንግ ኩባንያዎች ከቀረበው የኤሌክትሪክ ኃይል ከ220 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X