የሩሲያ የባቡር ፍንዳታ፦ አሁናዊ መረጃዎች
11:56 01.06.2025 (የተሻሻለ: 12:04 01.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ የባቡር ፍንዳታ፦ አሁናዊ መረጃዎች
የሀገሪቱ የምርመራ ኮሚቴ በሁለት ክልሎች ውስጥ ሁለት ድልድዮች ሆን ተብሎ በተፈጸመ ፍንዳታ መፍረሳቸውን ገልጿል።
በብራያንስክ ክልል፦
🟠 እንደ ሩሲያ ባለስልጣናት ገለጻ ከሆነ ከክሊሞቭ ወደ ሞስኮ ሲጓዝ የነበረ ባቡር የሀዲድ አመሻሹን መስመሩን ለቋል።
🟠 አደጋው የተከሰተው ባቡሩ በተደረመሰ የመንገድ ድልድይ ሥር ሲያልፍ ነው።
🟠 በዚህ አደጋ ቢያንስ ሰባት ሰዎች ሲሞቱ ህጻናትን ጨምሮ 66 ሰዎች ቆስለዋል። አርባ ሰባት ሰዎች ሆስፒታል ገብተዋል፤ የስምንት ወር ህጻን ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል።
🟠 የአካባቢው ገዥ በባቡር አደጋው የተጎዱ ሁሉም ተሳፋሪዎች ወዲያውኑ ወደ ህክምና ተቋማት ተወስደዋል ብለዋል። የተጎዱትን በአየር ጭምር ለማጓጓዝ የአስቸኳይ ጊዜ አምቡላንስ ቡድኖች ተደራጅተዋል።
በኩርስክ ክልል፦
🟠 እንደ የሩሲያ ምድር ባቡር ገለጻ የባቡር ድልድይ በከፊል በመደርመሱ ከጭነት ባቡር ጋር አደጋ ተከሰቷል።
🟠 አንድ የናፍታ ባቡር እና ሦስት ባዶ ፉርጎዎች ከሀዲድ ወጥተዋል።
🟠 የባቡሩ ሹፌር ጉዳት ደርሶበታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
