አፍሪኤግዚም ባንክ ለኢትዮጵያ የንግድ ማሕበረሰብ የሚያደርገውን ድጋፍ በማጠናከር በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ
15:13 31.05.2025 (የተሻሻለ: 15:34 31.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አፍሪኤግዚም ባንክ ለኢትዮጵያ የንግድ ማሕበረሰብ የሚያደርገውን ድጋፍ በማጠናከር በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ
የባንኩ የምሥራቅ አፍሪካ ክልላዊ ጽሕፈት ቤት ግንቦት 25 እና 26 “የኢትዮጵያን ዕድገት መደገፍ፡ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪያላይዜሽንን በአፍሪኤግዚም ባንክ መፍትሄዎች ማነቃቃት” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ ትርዒት ለማካሄድ አቅዷል።
ባንኩ ባለፉት አምስት ዓመታት በንግድ ፋሲሊቴሽን ፕሮግራሙ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት 4 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የሚገመት የንግድ ልውውጥ ማመቻቸቱን ገልጿል።
በ2024 የኢትዮጵያ ኩባንያዎች በባንኩ የንግድ ክፍያ አገልግሎቶች ፕሮግራም 32 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያላቸውን ዓለም አቀፍ የንግድ ክፍያዎች ፈፅመዋል።
53 የአፍሪካ ሀገራትን በአባልነት ያቀፈው ባንኩ ከኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ባለፈ ከሀገሪቱ የንግድ ማሕበረሰብ ጋር የላቀ ግኑኝነት ለመፍጠር እንዳቀደ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X