የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ከ55 ተቋማት ጋር ውህደት ፈፀመ
14:12 31.05.2025 (የተሻሻለ: 14:34 31.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ከ55 ተቋማት ጋር ውህደት ፈፀመ
ፋይዳ በሁሉም ክልሎች ተደራሽ እንዲሆን በመላ ሀገሪቱ ከአንድ ሺህ በላይ የምዝገባ ማዕከላት መቋቋሙን የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
አሁን ላይ ከ15 ነጥብ 99 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለፋይዳ እንደተመዘገቡም ተገልጿል።
በቀጣይ ስርዓቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአገልግሎት ሰጪዎች ዘንድ ለማስፋፋት እቅድ እንዳለ ፅህፈት ቤቱን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X