ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ አሸማጋይ ድርጅት መሥራች አባል ሆነች
12:56 31.05.2025 (የተሻሻለ: 13:14 31.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ አሸማጋይ ድርጅት መሥራች አባል ሆነች
በቻይና የሆንግ ኮንግ ልዩ አስተዳዳር በትናንትናው ዕለት በተካሄደ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት የዓለም አቀፍ አሸማጋይ ድርጅት በይነ መንግሥታዊ ተቋም መመሥረቱ ይፋ ሆኗል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ መሥራች አባል ሆና መፈረሟ በመንግሥታት መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች እና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ በሽምግልና ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም ተቋሙ በመንግሥታት፣ በመንግሥታትና በግሉ ዘርፍ መካከል የሚፈጠሩ ከኢንቨስትመንት ጋር የተያያዙ አለመግባባቶችን በሠላማዊ መንገድ በሽምግልና ለመፍታት ያቀደ መሆኑን አንስተዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X