በሱዳን ካርቱም ክፍለ ግዛት ከኮሌራ የሚያገግሙ ሰዎች ምጣኔ ወደ 92 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገለፀ
20:04 30.05.2025 (የተሻሻለ: 20:24 30.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሱዳን ካርቱም ክፍለ ግዛት ከኮሌራ የሚያገግሙ ሰዎች ምጣኔ ወደ 92 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሱዳን ካርቱም ክፍለ ግዛት ከኮሌራ የሚያገግሙ ሰዎች ምጣኔ ወደ 92 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገለፀ
መንግሥት የተከተለው አዲስ ስትራቴጂ ከፍተኛ መሻሻል ማምጣቱን የግዛቱ ጤና ሚኒስቴር የድንገተኛ አደጋ ህክምና ኮሚቴ አስታውቋል።
የኮሚቴው ዳይሬክተር ሞሐመድ አል-ቲጃኒ በዘረዘሩት ስትራቴጂ ውስጥ የተካተቱ ጉዳዮች፦
* በሽታው ወደ ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ከመዛመቱ በፊት ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድኖችን እና የመስክ ክሊኒኮችን ማሰማራት እና
* የበሽታው ስርጭት በታየባቸው አካባቢዎች የክትባት ዘመቻዎችን ማካሄድ ናቸው።
"በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ቀድሞ ለመለየት፣ ለማከም እና የሞት መጠኑን ለመቀነስ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት ወደ ሥራ እንዲገቡ እንዲሁም በሽታው በከፍተኛ ፍጥነት በተዛመተባቸው አካባቢዎች አራት የመጠለያ ማዕከላት እንዲቋቋሙ ተደርጓል” ሲሉ ተናግረዋል።
በካርቱም ዕለታዊ የሟቾች ቁጥር ማክሰኞ 28 የነበረ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ወደ 23 ዝቅ ብሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመላ ሀገሪቱ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ2 ሺህ 700 በላይ ሰዎች በኮሌራ ተይዘዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሱዳን ካርቱም ክፍለ ግዛት ከኮሌራ የሚያገግሙ ሰዎች ምጣኔ ወደ 92 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/