አሜሪካ ቦይንግ ላይ የተከፈተው የወንጀል ክስ እንዲዘጋ ጠየቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአሜሪካ ቦይንግ ላይ የተከፈተው የወንጀል ክስ እንዲዘጋ ጠየቀች
አሜሪካ ቦይንግ ላይ የተከፈተው የወንጀል ክስ እንዲዘጋ ጠየቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.05.2025
ሰብስክራይብ

አሜሪካ ቦይንግ ላይ የተከፈተው የወንጀል ክስ እንዲዘጋ ጠየቀች

የሀገሪቱ የፍትሕ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ ለ346 ሞት ምክንያት ከሆነው የማክስ አውሮፕላን መከስከስ ጋር ተያይዞ በግዙፉ የአሜሪካ ኩባንያ ላይ የቀረበውን የማጭበርበር ወንጀል ክስ እንዲዘጋ ጠይቋል።

በትናንትናው ዕለት ቀርቧል የተባለው ይህ ጥያቄ የአውሮፕላን አምራቹ የፌደራል አቪየሽን ባለሥልጣናት የሚያካሄዱትን ምርመራ በማደናቀፍ ከቀረበበት ክስ ለማምለጥ ስምምነት ላይ መድረሱን ተከትሎ የመጣ ነው።

ቦይንግ ክሱን ለማዘጋት ለተጎጂ ቤተሰቦች የሚሰጠውን ተጨማሪ 445 ሚሊየን ዶላር ጨምሮ በአጠቃላይ ከ1.1 ቢልየን ዶላር በላይ ለመክፈል መስማማቱን የአሜሪካ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

በአደጋው ሴት ልጃቸውን ያጡት ናዲያ ማሌሮን የአሜሪካ መንግሥት ስምምነቱ "እውነተኛ ተጠያቂነትን" ያመጣል በማለቱ ማዘናቸውን ገልፀው "በስምምነቱ ምክንያት ተጠያቂ አይኖርም" ብለዋል።

ቦይንግ ሰራሾቹ ማክስ 737 አውሮፕላኖች በጥቅምት 2011 ዓ.ም በኢንዶኔዥያ በተመሳሳይ አመት መጋቢት ወር አዲስ አበባ አቅራቢያ መከስከሳቸው የሚታወስ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0