የሩሲያ ተደራዳሪ ልዑካን ቡድን በኢስታንቡል ከኪዬቭ አቻው ጋር ለሚያደርገው የሁለተኛ ዙር ድርድር እንደሚዘጋጅ ክሬምሊን ገለጸ
13:54 30.05.2025 (የተሻሻለ: 15:14 30.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ተደራዳሪ ልዑካን ቡድን በኢስታንቡል ከኪዬቭ አቻው ጋር ለሚያደርገው የሁለተኛ ዙር ድርድር እንደሚዘጋጅ ክሬምሊን ገለጸ
ሞስኮ የሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ስምምነት ረቂቅ በሁለተኛው ዙር ድርድር ውይይት ይደርግበታል ብላ ተስፋ ታደርጋለች ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡
በዲሚትሪ ፔስኮቭ መግለጫ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
▪ ዩክሬን ግጭት አፈታትን አስመልክቶ የሩሲያ ረቂቅ የስምምነት ዝርዝሮች ለሕዝብ ይፋ አይደረጉም።
▪ ፑቲን ከዘለንስኪ እና ከትራምፕ ጋር በግል የመገናኘት ሀሳብን ይደግፋሉ፤ ነገር ግን ከፍተኛ ዝግጅት እንደሚያስፈልገው አጽንዖት ሰጥተዋል።
▪ የአውሮፓ ደህንነት የወደፊት እጣ ፈንታ ያስመለከተ ውይይት መደረግ ያለበት ከአውሮፓውያን ጋር ነው፤ በኢስታንቡል የሚደረገው ንግግር በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ነው።
▪ ፑቲን በምስራቅ አቅጣጫ የኔቶ መስፋፋትን በተመለከተ አሜሪካን ጨምሮ ለተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት በተደጋጋሚ የሞስኮን አቋም አስተላልፈዋል።
▪ ሞስኮ ዋሽንግተን የኔቶን መስፋፋት በተለይም በሽምግልናው ላይ ሊኖረው የሚችለውን ሚና በተመለከተ የሩሲያን ስጋት መረዳቷን በበጎው ትቀበላለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X