ኢራን የዩራኒየም ማበልፀጊያዋ ለአንድ ዓመት እንደታገደ የሚገልጹ ዘገባዎችን አስተባበለች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢራን የዩራኒየም ማበልፀጊያዋ ለአንድ ዓመት እንደታገደ የሚገልጹ ዘገባዎችን አስተባበለች
ኢራን የዩራኒየም ማበልፀጊያዋ ለአንድ ዓመት እንደታገደ የሚገልጹ ዘገባዎችን አስተባበለች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.05.2025
ሰብስክራይብ

ኢራን የዩራኒየም ማበልፀጊያዋ ለአንድ ዓመት እንደታገደ የሚገልጹ ዘገባዎችን አስተባበለች

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋሄ ዩራኒየም ማበልፀግ "የሀገሪቱ የኒውክሌር ኢንዱስትሪ ወሳኝ አካል ነው" ብለዋል።

አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን አሜሪካ ዩራኒየምን ለሰላማዊ አገልግሎት የማጣራት መብቷን ከተቀበለች እና የታገዱ የኢራን ንብረቶችን ከለቀቀች ኢራን ዩራኒየም ማበልፀጓን ልታቆም እንደምትችል በዛሬው ዕለት ዘግበዋል።

ቃል አቀባዩ "ኢራን የማዕቀቦች መንሳት አሜሪካ በትክክል ድርድር ለማድረግ ፍላጎት እንዳላት የምትገመግበት ቁልፍ መለኪያ ነው" ብለዋል።

ኢራን እና አሜሪካ በቴህራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ በኦማን አሸማጋይነት አምስት ዙር ንግግሮችን አድርገዋል። የመጨረሻው ዙር ግንቦት 15 ቀን ሮም ውስጥ ተካሂዷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0