ምዕራባውያን በታውረስ ሚሳኤል አማካኝነት የሩሲያን "ትዕግስት መፈተን" እና መተንኮስ ፈልገዋል ሲሉ የማሊ ባለሥልጣን ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱምዕራባውያን በታውረስ ሚሳኤል አማካኝነት የሩሲያን "ትዕግስት መፈተን" እና መተንኮስ ፈልገዋል ሲሉ የማሊ ባለሥልጣን ተናገሩ
ምዕራባውያን በታውረስ ሚሳኤል አማካኝነት የሩሲያን ትዕግስት መፈተን እና መተንኮስ ፈልገዋል ሲሉ የማሊ ባለሥልጣን ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.05.2025
ሰብስክራይብ

ምዕራባውያን በታውረስ ሚሳኤል አማካኝነት የሩሲያን "ትዕግስት መፈተን" እና መተንኮስ ፈልገዋል ሲሉ የማሊ ባለሥልጣን ተናገሩ

የአውሮፓ ድጋፍ ሩሲያ ያላትን የመከላከያ እና ጥቃት አቅም ሙሉ በሙሉ እንድትጠቀም ለማስገደድ የሚደረግ ሙከራ ነው ሲሉ የማሊ ፕሬዝዳንት አማካሪ አዳማ ዲያባቴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

እንዲህ ያለው ቅስቀሳ የሚያስከትለው መዘዝ ምንድን ነው?

ይህ ጫና ሩሲያ ወታደራዊ ኃይሏን እንድታጠናከር ነው ያደረገው ሲሉ ባለሥልጣኑ ተናግረዋል፡፡ አክለውም የሩሲያ ጦር አሁናዊ ቁመና "ከየትኛውም የምዕራባውያን ሠራዊት የበለጠ በጦርነት የጠነከረ እና ለጦርነት የተዘጋጀ ነው" ብለዋል።

እንደ አማካሪው ገለጻ ጀርመን በታውረስ ሚሳኤሎቿ በዩክሬን ጉዳይ ግንባር ቀደም ለመሆን ከፈረንሳይ ጋር እየተፎካከረች ነው።

"ሁሉም አለቃ እና ቀዳሚ እሳት ለኳሽ መሆን ይፈልጋል። በአውሮፓውያን ሀገራት መካከል ያለው ፉክክር ከሩሲያ ጋር ካለው ያነሰ አይደለም። ፉክክራቸውም ጤናማ አይደለም" ሲሉ ዲያባቴ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0