አፍሪካ 1 ነጥብ 86 ትሪሊዮን ዶላር ዕዳ ውስጥ ተዘፍቃለች ፤ ነገር ግን ነፃ በመውጣት የራሷን ኢኮኖሚ መገንባት ትችላለች
16:55 29.05.2025 (የተሻሻለ: 17:14 29.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አፍሪካ 1 ነጥብ 86 ትሪሊዮን ዶላር ዕዳ ውስጥ ተዘፍቃለች ፤ ነገር ግን ነፃ በመውጣት የራሷን ኢኮኖሚ መገንባት ትችላለች
“አብዛኛው የአህጉሪቱ በጀት ለዕዳ ክፍያ ይውላል። የቀረው በሀገር ውስጥ ሌሎች ተግባራትን ለመደገፍ የሚውል ነው" ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ዋና ፀሀፊ ክላቬር ጋቴቴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
እንደ ዋና ፀሃፊው ገለጻ ተግዳሮቶቹን በሚከተሉት እርምጃዎች መቅረፍ ይቻላል፦
የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓትን በማሻሻል፤ ሁሉንም አበዳሪዎች ወደ ድርድር ጠረጴዛው በማምጣት፣
የሀገር ውስጥ ሀብት አሰባሰብን በማሳደግ፤ የተበላሹ የታክስ ስርዓቶችን በማስተካከል እና ጠንካራ የካፒታል ገበያዎችን በመገንባት፣
አፍሪካውያን በባለቤትነት የሚመሯቸውን ገበያዎች በመፍጠር፤ በእርስ በእርስ ንግድ እና ኢንቨስትመንት የአፍሪካን እድገት በማጠናከር፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X