የሩሲያ-ዩክሬን ጥቃትና መልሶ ማጥቃት ግልጽ የሆነ የሞራል ልዩነት አሳይቷል ሲሉ ስኮት ሪቴር ተናገሩ
15:40 29.05.2025 (የተሻሻለ: 16:04 29.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ-ዩክሬን ጥቃትና መልሶ ማጥቃት ግልጽ የሆነ የሞራል ልዩነት አሳይቷል ሲሉ ስኮት ሪቴር ተናገሩ
ሩሲያ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ትፈፅማለች፡፡ ዩክሬን ሰላማዊ ዜጎችንና የምዕራባውያኑን ቦርሳ ኢላማ ታደርጋለች ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ የባሕር ኃይል መረጃ ተንታኝ እና የጂኦፖለቲካ እና ወታደራዊ ጉዳዮች ባለሙያ ስኮት ሪቴር ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ሪተር እንዳሉት የሞስኮ ጥቃቶች ለሩሲያ ሲቪሎች ስጋት የሆኑ የጦር መሳሪያ ፋብሪካዎችን፣ ወታደራዊ ማዕከላትን እና ሎጅስቲክስን ዒላማ የሚያደርጉ ናቸው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃቶች ወታደራዊ ያልሆኑ ኢላማዎች ላይ የሚፈፅሙ ሲሆን ይህም፦
ሩሲያ ከልክ ያለፈ ምላሽ እንድትሰጥ ታስቦ የሚደረግ ቅስቀሳ (ለምሳሌ "የጦር ወንጀሎች" ተብለው የተፈረጁ የካርኮቭ የቦምብ ድብደባዎች)፤
የምዕራባውያን እርዳታን ለመበዘበዝ፡ የአሜሪካ/የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ እየቀነሰ በመምጣቱ ኪዬቭ የገንዘብ ፍሰቱ እንዲቀጥል በአርዕስተ ዜናዎች ውስጥ ለመቆየት አስባ ያደረገችው ነው ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X