ኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ለማዋሃድ አቅዳለች
15:09 29.05.2025 (የተሻሻለ: 15:24 29.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ለማዋሃድ አቅዳለች
ቴክኖሎጂውን በዘላቂነት ለመተግበር የትምህርት ሚኒስቴር ለ34 ሺህ የከፍተኛ ትምህርት መምህራን ሰፊ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
በትምህርት ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዋና ዳይሬክተር ዘላለም አሰፋ ተማሪዎችና አስተማሪዎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት እውቀት ሊናራቸው ይገባል ብለዋል።
ቴክኖሎጂው ተማሪዎችን ለመከታተል፣ ኩረጃን ለማስቀረት እና በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ተዓማኒነትን ለማዳበር ሥራ ላይ እንደሚውል ለሀገር ውስጥ የቴሌቪዥን ጣቢያ ገልጸዋል።
እቅዱ ከአሪዞና ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው ተብሏል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X