ኢትዮጵያ የደቡባዊውን ዓለም ፍላጎት ችላ ያለ የዓለም አቀፍ መዋቅር ማሻሻያ ለውድቀት የተጋለጠ ነው አለች
13:56 29.05.2025 (የተሻሻለ: 14:14 29.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የደቡባዊውን ዓለም ፍላጎት ችላ ያለ የዓለም አቀፍ መዋቅር ማሻሻያ ለውድቀት የተጋለጠ ነው አለች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የደቡባዊውን ዓለም ፍላጎት ችላ ያለ የዓለም አቀፍ መዋቅር ማሻሻያ ለውድቀት የተጋለጠ ነው አለች
በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 13ኛው የደህንነት ጉዳዮች የከፍተኛ ባለሥልጣናት ዓለም አቀፍ ስብስባ ላይ የተናገሩት ነው።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አዲሱ የፀጥታ አርክቴክቸር እኩል እና የማይከፋፈል መሆን አለበት ሲሉ በስብሰባው መክፈቻ ላይ ተናግረው ነበር።
አምባሳደር ገነት አክለውም የሰው ሰራሽ አስተውሎት እድገት እና እየጨመረ የመጣው የሳይበር ቴክኖሎጂ ስጋት ለደቡባዊው ዓለም ከባድ የደህንነት ተግዳሮቶችን እየፈጠሩ እንደሆነ አንስተዋል።
በዚህ በኩል የብሪክስ የሳይበር አደጋ ምላሽ ቡድንን ለማጠናከር የአባል ሀገራቱ ትብብር እጅግ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል ሲል ኤምባሲው አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X