ሩሲያ ግንቦት 25 እንዲደረግ ያቀረበችውን የውይይት እቅድ በተመለከተ ከዩክሬን ምላሽ እየጠበቀች ነው ሲል ክሬሚሊን ገለፀ
13:27 29.05.2025 (የተሻሻለ: 13:44 29.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ ግንቦት 25 እንዲደረግ ያቀረበችውን የውይይት እቅድ በተመለከተ ከዩክሬን ምላሽ እየጠበቀች ነው ሲል ክሬሚሊን ገለፀ
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንደተናገሩት ሞስኮ የመፍትሄ ሃሳቦቹን ይዘት ይፋ አታደርግም፤ ድርድሩ ሚስጥራዊነቱ ተጠብቆ መቀጠል አለበት።
የመግለጫው ዋና ዋና ይዘቶች ፦
▪ኪዬቭ የስምምነቱን ረቂቅ ሩሲያ በፍጥነት እንድታስረክብ ያቀረበችው ጥያቄ ገንቢ አይደለም።
▪ኪዬቭ ለንግግር ዝግጁነቷን ታረጋገጥ።
▪ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሚደረገው ቀጥተኛ ድርድር መቀጠሉ አስፈላጊ ነው።
▪ በሩሲያ ፕሬዝዳንት ረዳት ሜዲንስኪ ላይ የተሰነዘሩት ማስፈራሪያዎች አስነዋሪ ናቸው፤ ሞስኮ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አስፈላጊውን ምርመራ ታካሂዳለች።
▪በአሁኑ ጊዜ በፑቲን እና በትራምፕ መካከል አዲስ ውይይት የማድረግ ዕቅድ የለም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X