⭐ በአዲስ አበባ 11 ሆቴሎች የባለ 5 ኮከብ ደረጃ ተሰጣቸው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ⭐ በአዲስ አበባ 11 ሆቴሎች የባለ 5 ኮከብ ደረጃ ተሰጣቸው
⭐ በአዲስ አበባ 11 ሆቴሎች የባለ 5 ኮከብ ደረጃ ተሰጣቸው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.05.2025
ሰብስክራይብ

በአዲስ አበባ 11 ሆቴሎች የባለ 5 ኮከብ ደረጃ ተሰጣቸው

የቱሪዝም ሚኒስቴር አዲስ አበባ በሚገኙ 92 ሆቴሎች ላይ ሲያደርግ የቆየውን የደረጃ ምደባ ውጤት ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የምደባው ውጤት፦

በመዲናዋ ከተመዘኑ 92 ሆቴሎች ውስጥ 40 የሚሆኑት ብቻ በተለያየ እርከን የኮከብ ደረጃዎችን አግኝተዋል፡፡

በምዘናው መሠረት 11 ሆቴሎች ባለ 5 ኮከብ፣ 9 ሆቴሎች ባለ 4 ኮከብ፣ 7 ሆቴሎች ባለ 3 ኮከብ፣ 5 ሆቴሎች ባለ 2 ኮከብ እና 2 ሆቴሎች ባለ 1 ኮከብ ሆነው ተመድበዋል፡፡

ከ40ዎቹ ሆቴሎች ውስጥ 34 የሚሆኑት ዳግም ምደባ የተሰጣቸው ሲሆን 6 የሚሆኑት ለዘርፉ አዲስ ናቸው።

የኮከብ ምደባው ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት ብቻ እንደሚያገለግል ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0