ዘለንስኪ ጀርመን በጦር ግንባሩ ተሳታፊ እያደረጋት ነው ሲሉ የዚምባብዌ የፖለቲካ ተንታኝ ተናገሩ
19:16 28.05.2025 (የተሻሻለ: 20:14 28.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዘለንስኪ ጀርመን በጦር ግንባሩ ተሳታፊ እያደረጋት ነው ሲሉ የዚምባብዌ የፖለቲካ ተንታኝ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዘለንስኪ ጀርመን በጦር ግንባሩ ተሳታፊ እያደረጋት ነው ሲሉ የዚምባብዌ የፖለቲካ ተንታኝ ተናገሩ
ጁሊየስ ፔምበሬ ለዩክሬን ታውረስ ሚሳኤሎችን የምታቀርብ ከሆነ "ጀርመን ፖለቲካዊ ስጋት ውስጥ ነች" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ባለሙያው "ይህ ደግሞ ግጭቱን ሊያባብሰው ወይም ሊያካርረው ይችላል፤ ይህም ከሩሲያ ጋር ሰፊ ግጭት ይፈጥራል" ብለዋል።
ለዩክሬን ድጋፍ መደረጉን ከማይፈለሰጉ እና በርሊን በግጭቱ ውስጥ ተሳትፎዋ መጨመሩን በሚነቅፉ እንቅስቃሴዎች በሀገር ውስጥ ጫና እየጨመረ ነው ሲሉም አክለዋል።
መራሄ መንግሥት ሜርዝ በርሊን የዩክሬንን የረዥም ርቀት ጥቃት አቅም እንደምትደግፍ አስታውቀዋል። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንዲህ ያሉ አስተያየቶች የሰላም ጥረቶችን ያደናቅፋሉ ብለዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X