#viral| የእስራኤል አምባሳደር ከሴኔጋል ኮሌጅ ውስጥ በፍልስጤም ደጋፊዎች ተባረሩ
18:10 28.05.2025 (የተሻሻለ: 18:34 28.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
#viral| የእስራኤል አምባሳደር ከሴኔጋል ኮሌጅ ውስጥ በፍልስጤም ደጋፊዎች ተባረሩ
የእስራኤል አምባሳደር ዩቫል ዋክስ ተማሪዎች ባሰሙባቸው ተቃውሞና ፍልስጤምን የሚደግፉ መፈክሮች በዳካር ከሚገኘው ዩኒቨርስቲ ካምፓስ ለመውጣት ተገደዋል።
ዋክስ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ዙሪያ ንግግር እንዲያደርጉ በሀገሪቱ ትልቁና ታዋቂ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ቺክ አንታ ዲዮፕ ዩኒቨርሲቲ ተጋብዘው እንደተገኙ ታውቋል።
በርካታ ተማሪዎች ግን እሳቸው እንደደረሱ "ፍልስጤምን ነፃ አውጡ" "ጋዛን ነፃ አውጡ" እና "እስራኤል የጦር ወንጀለኛ ናት" እያሉ በመጮህ ከአዳራሹ ውጭ መሰብሰባቸው ተገልጿል።
የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዋክስ ንግግሩን ሳያደርጉ በጸጥታ አስከባሪዎች ታጅበው ግቢውን ለቀው ሲወጡ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች በስፋት ተሠራጭተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X