የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚቀጥሉት ወራት ሁለት የሀገር ወስጥ አየር ማረፊያዎችን ግንባታ አጠናቆ ሥራ አንደሚያስጀምር ገለፀ
16:23 28.05.2025 (የተሻሻለ: 16:44 28.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚቀጥሉት ወራት ሁለት የሀገር ወስጥ አየር ማረፊያዎችን ግንባታ አጠናቆ ሥራ አንደሚያስጀምር ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚቀጥሉት ወራት ሁለት የሀገር ወስጥ አየር ማረፊያዎችን ግንባታ አጠናቆ ሥራ አንደሚያስጀምር ገለፀ
በተጨማሪም አየር መንገዱ በቢሾፍቱ የሚገነባውን ግዙፍ ኤርፖርት በመጪው ዓመት ህዳር ወር ለመጀመር የዝግጅት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ መስፍን ጣሰው አስታውቀዋል።
ግዙፉ የአፍሪካ አየር መንገድ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 14 ሚሊየን 500 ሺሕ የሚጠጉ መንገደኞችን እንዳጓጓዘም ኃላፊው ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
በዚህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የስምንት በመቶ ብልጫ ያለው 5.6 ቢሊየን ዶላር ገቢ መሰብሰቡን ጨምረው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X