"ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ቀዳሚዎቹ ተጠያቂዎች ምዕራባውያን ናቸው"

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ቀዳሚዎቹ ተጠያቂዎች ምዕራባውያን ናቸው"
ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ቀዳሚዎቹ ተጠያቂዎች ምዕራባውያን ናቸው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.05.2025
ሰብስክራይብ

"ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ቀዳሚዎቹ ተጠያቂዎች ምዕራባውያን ናቸው"

ምዕራባውያን ኢኮኖሚያቸውን በየትኛውም መንገድ ማሳደግ እንጂ አካባቢ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ያስጨንቃቸው እንዳልነበር የዲፌንድ ኢንቫይሮመንት ግብረ ሰናይ ድርጅት መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ መልካሙ አጎ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"ምዕራባውያን ዛሬ ለደረሱበት የኢኮኖሚ ደረጃ የተከፈለ ዋጋ አለ። የተፈጥሮ ሀብት፣ አካባቢ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ምክንያቶቹ እነርሱ ናቸው፡፡"

በሌላ በኩል የአየር ንብረት ለውጥን አጀንዳ እያደረጉ በሚቆጣጠሯቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት በኩል ለመጠምዘዣ እየተጠቀሙበት እንደሆነ ጠቁመዋል።

"በጣም ነው እንጂ የሚጠመዘዘው፤ ግልጽ እኮ ነው። ስለ የአካባቢ አየር ንብረት ለውጥ በምናወራበት ጊዜ፤ ምክንያት አለ ውጤት አለ" ብለዋል።

በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ በጣም ትልቅ የፖለቲካ አጀንዳና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራት ጡንቻቸውን የሚፈታተሹበት እንደሆነ ተናግረዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0