ከሩሲያ ጋር የሚደረግ የዲጂታል ዘርፍ ትብብር ኢትዮጵያን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ባለሙያው ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከሩሲያ ጋር የሚደረግ የዲጂታል ዘርፍ ትብብር ኢትዮጵያን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ባለሙያው ተናገሩ
ከሩሲያ ጋር የሚደረግ የዲጂታል ዘርፍ ትብብር ኢትዮጵያን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ባለሙያው ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.05.2025
ሰብስክራይብ

ከሩሲያ ጋር የሚደረግ የዲጂታል ዘርፍ ትብብር ኢትዮጵያን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ባለሙያው ተናገሩ

የሁለቱ ሀገራት ቅንጅት የደህንነት መረጃዎችን ለመጋራት ይጠቅማል ሲሉ ከፍተኛ የሶፍትዌር መሃንዲስ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ገንቢ አቤል በነበሩ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ላይ ተናግረዋል።

"ለምሳሌ ሩሲያ ጋር የተገኘ ራንሰምዌር፣ ማልዌር ቢኖር ኢንተለጀንሱ (የመረጃ ተቋማት) መተባበር እስከቻሉ ድረስ አንተን ሳያጠቃህ ቀድመህ ልትከላከል ትችላለህ፡፡ ሌላው በጋራ ምርምሮችን ልትሠራ ትችላለህ፡፡  ሁለተኛ ፖሊሲን ከጊዜው ጋር የሚሄድ አድርጎ ለመቅረጽ ሊያግዝ ይችላል፡፡"

በሌላ በኩል ባለሙያው የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ በመሠረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል።

“የመጀመሪያው ነገር የመሠረተ ልማት ጥገኘነታችንን መቀነስ ነው፡፡ ለምሳሌ አሁን ላይ የምንጠቀማቸው የመረጃ ማዕከላት ከምዕራባውያን ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ ለነዚህ ነገሮች መፍትሄ መሰጠት አለበት። ለምሳሌ አፍሪካውያን የራሳቸው የመረጃ ማዕከል ቢኖራቸው፤ በዚህ ረገድ ኢትዮ ቴሌኮም የራሱን ክላውድ መሠረተ ልማት ገንብቶ ለተጠቃሚዎች እያቀረበ ነው፡፡ እንደዚህ ዐይነት ነገሮች ቢበዙ እንደ አፍሪካ መረጃዎች በሶስተኛ አካል የመውጣቱ ዕድል ይቀንሳል" ሲሉ ተናግረዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0