ፈረንሳይ ከምዕራብ አፍሪካ ወታደሮቿን ማስወጣቷን ተከትሎ አሜሪካ እና እንግሊዝ የቀድሞ የፈረንሳይ ወታደሮችን በአካባቢው እየቀጠሩ እንደሆነ ተዘገበ
17:33 27.05.2025 (የተሻሻለ: 17:54 27.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ፈረንሳይ ከምዕራብ አፍሪካ ወታደሮቿን ማስወጣቷን ተከትሎ አሜሪካ እና እንግሊዝ የቀድሞ የፈረንሳይ ወታደሮችን በአካባቢው እየቀጠሩ እንደሆነ ተዘገበ
አንድ የፈረንሳይ ቻናል ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው የአሜሪካ እና የእንግሊዝ የግል ወታደራዊ ድርጅቶች ፈረንሳይ ከቀጣናው ለቃ በመውጣቷ የተፈጠረውን “ክፍተት እየሞሉ” ናቸው።
ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የፈረንሳይ ወታደራዊ አመራር የቀድሞ ወታደሮች በአካባቢው መገኘታችው ፓሪስ በተዘዋዋሪ እየተሳተፈች ነው የሚል ትርጓሜ እንዳይሰጠው ሰግቷል፡፡
የፈረንሳይ ከክልሉ ለቆ የመውጣት ሂደት እሳካሁን ምን ይመስላል፦
▪ከቻድ ከጥር ወር ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ወጥታለች፡፡
▪ከሴኔጋል እስከ 2025 መጨረሻ ድረስ ለመውጣት ታቅዷል፡፡
▪ከማሊ (በ2022)፣ ከቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር (በ2023) ወጥታለች፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሳህል ሀገራት ጥምረት የቀጣናውን የፀጥታ ችግሮች ለመፍታት ያለመ የጋራ ወታደራዊ ኃይል እያቋቋም ነው።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X