የቻይና ባሕል ተሳትፎ በኢትዮጵያ እያደገ መምጣቱ ተነገረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየቻይና ባሕል ተሳትፎ በኢትዮጵያ እያደገ መምጣቱ ተነገረ
የቻይና ባሕል ተሳትፎ በኢትዮጵያ እያደገ መምጣቱ ተነገረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.05.2025
ሰብስክራይብ

የቻይና ባሕል ተሳትፎ በኢትዮጵያ እያደገ መምጣቱ ተነገረ

በአዲስ አበባ ተካሂዶ የነበረው 24ኛው "ቻይኒዝ ብሪጅ" የቋንቋ ውድድር ቻይናን ከዓለም ዓቀፉ ማሕብረሰብ ጋር ያገናኘ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ተናግረዋል።

"ተወዳዳሪዎቹ የቻይና ቋንቋ ብቃታቸውን እና የጥበብ ተሰጥኦቸውን ሲያሳዩ እና ለቻይና ባሕልና ሕዝብ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር ሲገልጹ ማየት በጣም ያስደስታል" ብለዋል አምባሳደር ቼን።

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስትር ደኤታ ሰለሺ ግርማ ዝግጅቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል እያደገ የመጣውን የባሕል ልውውጥ የሚያሳይ ነው በማለት አወድሰውታል ሲል ሺንዋ ዘግቧል።

"ቋንቋ መማር የመጀመሪያው እርምጃ እና ለእድገት ቁልፍ ነው። በኢትዮጵያ ተወዳዳሪዎች የቀረቡት የባሕል ትርዒቶች በኢትዮጵያና በቻይና መካከል እያደገ የመጣው የባሕላዊ ትስስር አንዱ መገለጫ ነው" ብለዋል።

በርካታ ኢትዮጵያውያን ስለ ቻይና ቋንቋ እና ባሕል ለማወቅ ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0