የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪና ዘርፍ የባትሪ አወጋገድ እና መልሶ ጥቅም ላይ ማዋልን ትኩረቱ ሊያደርግ እንደሚገባ ባለሙያው አመላከቱ
21:44 26.05.2025 (የተሻሻለ: 22:44 26.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪና ዘርፍ የባትሪ አወጋገድ እና መልሶ ጥቅም ላይ ማዋልን ትኩረቱ ሊያደርግ እንደሚገባ ባለሙያው አመላከቱ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪና ዘርፍ የባትሪ አወጋገድ እና መልሶ ጥቅም ላይ ማዋልን ትኩረቱ ሊያደርግ እንደሚገባ ባለሙያው አመላከቱ
የመኪና ቴክኖሎጂ ባለሙያው ሞገስ ነጋሽ ኢትዮጵያ እየተከተለችው ያለው የኤሌክትሪክ መኪና ፖሊሲ በአግባቡ የሚተገበር ከሆነ ሀገሪቱን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"የነዳጅ መኪናዎች አብዛኛዎቹ ያረጁ ናቸው። ገዢዎችም በመኪናዎቹ ብልሽት ይሠቃያሉ። በተጨማሪም የነዳጅ ወጪ እና ወረፋ ችግር አለ። አሁን ነገሮች እየተለወጡ ነው። የኤሌክትሪክ መኪኖች የጠቀስኳቸውን ችግሮች እየቀነሱ ነው" ብለዋል።
ባለሙያው በዘርፉ የሰለጠኑ በቂ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
"ኢትዮጵያ ውስጥ የሰለጠኑ እና የተማሩ ሰዎች አሉን። የሚያስፈልገን የቴክኖሎጂ ሽግግር እና አንዳንድ ስልጠናዎች ናቸው።
አክለውም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሠረተ ልማቶችን በተለይም የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን በሀገሪቱ የከተማ እና የክልል አካባቢዎች ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን አስረድተው ለዚህም መንግሥትና የግል ባለሀብቱ በቅንጅት መሥራት አለባቸው ብለዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X