በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ጤና ሚኒስቴር ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ጤና ሚኒስቴር ገለፀ
በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ጤና ሚኒስቴር ገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.05.2025
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ጤና ሚኒስቴር ገለፀ

ቫይረሱ በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ እንደተገኘ የሚኒስቴሩ መግለጫ አመልክቷል። በተላላፊ በሽታው የ21 ቀን እድሜ ያለው ህጻን እና እናቱ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል።

ለስርጭቱ ምክንያት ይሆናል ተብሎ የተጠረጠረው የወጣቱ አባት ወደ ጎረቤት ሀገር ሄዶ እንደነበር ተገልጿል።

በተጨማሪም የሄደባቸውን አካባቢዎች እንዲሁም ከግለሰቡ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች የመለየትና ክትትል የማድረግ ሥራ ተጀምሯልም ተብሏል።

በቫይረሱ ተይዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በለይቶ ማቆያ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው ሲል የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኤምፖክስ በሽታ ሽፍታ፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ የራስ ምታት፣ ድካም እና የጀርባ ሕመም ያስከትላል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0