ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት ከብሔራዊ ጥቅሟ ጋር የተሳሰረ እንደሆነ ገለፀች
17:37 25.05.2025 (የተሻሻለ: 17:54 25.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት ከብሔራዊ ጥቅሟ ጋር የተሳሰረ እንደሆነ ገለፀች
ይሄ የተገለፀው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና ምክትል ፕሬዝዳንቱ ቤንጃሚን ቦልሜል ጋር በጁባ ባደረጉት ውይይት ነው።
የልዑካን ቡድኑ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ መልዕክትም አድርሷል፡፡
የሀገር ውስጥ ሚዲያ እንደዘገበው ልዑኩ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X