ኢትዮጵያ የማር ምርቷን የሚቀበሉ ሀገራት ለጥራት ማረጋገጫ ላብራቶሪዋ ዕውቅና እንዲሰጡ ጠየቀች
13:36 25.05.2025 (የተሻሻለ: 13:54 25.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የማር ምርቷን የሚቀበሉ ሀገራት ለጥራት ማረጋገጫ ላብራቶሪዋ ዕውቅና እንዲሰጡ ጠየቀች
ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ወደ ውጭ የምትሸጠውን ማር ጥራት ለማረጋገጥ ጀርመን ትልክ እንደነበር ግብርና ሚኒስቴር ገልጿል።
አሁን ላይ ብዙ ወጪ ያስወጣ የነበረውን ይሄን ሂደት የሚያስቀር የማር ምርት ጥራት ማረጋገጫ ላብራቶሪ በጥራት መንደር ውስጥ ተቋቋሟል።
የማር ምርትን ከአማራረት ጀምሮ ጥራቱን የማስጠበቅ ሥራ በሀገር ውስጥ አቅም እየተከናወነ ነው ሲል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ በአማካኝ 500 ሺህ ቶን ማር፣ 50 ሺህ ቶን የንብ ሰምና 500 ቶን የንብ ሙጫ የማምረት አቅም አላት።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X