ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀረበ
20:16 24.05.2025 (የተሻሻለ: 20:34 24.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀረበ
የኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስትቲዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ አብዮት ብርሃኑ በአካባቢ ጥበቃ መንገድ ጠራጊ የሚባሉት ሩሲያዊው ኢቫኖቪች ቫቪሎቭ የኢትዮጵያን የአዝርዕት ዓይነቶች ያጠኑና የሰበሰቡ ቀዳሚው ሰው ናቸው ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በቫቪሎቭ የብርቅዬ አዝርዕት መገኛ ማዕከል ውስጥ ከተካተቱ ሀገራት አንዷ እንደሆነችም ገልጸዋል።
ለዚህም ሩሲያን እና የሩሲያን ሕዝብ እናመሰግናለን ያሉት አቶ አብዮት ሁለቱ ሀገራት ትበብሩን መቀጠል አለባቸው ብለዋል።
"በብዝሃ ሕይወት ጥበቃ የነበረውን ስኬታማ ትብብር ለማስቀጠል እና ተጨማሪ አስፈላጊ የምርምር ማዕከላትን እንድናቋቁም ለሩሲያ መንግሥት ጥሪ አቀርባለሁ።"
በሌላ በኩል የብሪክስ ሀገራት በኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ትብብር ማድረጋቸው "አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ነው" ሲሉ አስረግጠዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X