ቡርኪና ፋሶ ኃያላን ሀገራት "ለሽብርተኝነት የሚያደርጉትን ድጋፍ" አወገዘች
19:05 24.05.2025 (የተሻሻለ: 19:24 24.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቡርኪና ፋሶ ኃያላን ሀገራት "ለሽብርተኝነት የሚያደርጉትን ድጋፍ" አወገዘች
ጠቅላይ ሚኒስትር ሪምታልባ ዣን ኢማኑኤል ኡድራጎ በምዕራብ አፍሪካ እና ሳህል ከተመድ ተወካይ ሊዮናርዶ ሳንቶስ ሲማኦ ጋር በትናንትናው ዕለት ተወያይተዋል።
በኡጋዱጉ በተደረገው ስብሰባ ኡድራጎ ሽብርተኝነት እየተወሳሰበ እና ሕጻናትንም ጭምር እየተጠቀመ እንደመጣ ተናግረዋል።
አክለውም ተመድ ለሉዓላዊነታቸው የቆሙ ሀገራትን መደገፍ እና ለአሸባሪዎች አሻሚ ስያሜ በመስጠት ሽፋን መሆኑን ማቆም አለበት ብለዋል።
ሲማኦ በበኩላቸው ተመድ የኑሮ ሁኔታዎችን ለማሻሻል ቁርጠኛ እንደሆነ አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/