የአፍሪካ ቀንድ እና የባሕረ ሰላጤው ሀገራት ትብብራቸውን ለማጠናከር ወሳኝ ግዜ ላይ እንደሆኑ ተመራማሪው ጠቆሙ
18:19 24.05.2025 (የተሻሻለ: 18:34 24.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ቀንድ እና የባሕረ ሰላጤው ሀገራት ትብብራቸውን ለማጠናከር ወሳኝ ግዜ ላይ እንደሆኑ ተመራማሪው ጠቆሙ
ከሶስተኛው የአፍሪካ ቀንድ እና የኤደን ባሕረ ሰላጤ ሀገራት ውይይት ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቆይታ ያደረጉት በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አማረ ቀናው የቀጣናው ሀገራት ዘርፈ ብዙ ትብብር ማድረግ እንደሚችሉ አስረድተዋል።
"ኃያላኖቹ አፍሪካ ሁሌም የእነሱ ብቻ እንደምትሆን በማሰብ በአፍሪካ ቀንድ ለረጅም ጊዜ ቆይተዋል። አሁን ላይ በተለይም የባሕረ ሰላጤው ሀገራት ተነሳስተዋል። በአፍሪካ ቀንድ በኢንቨስትመንት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እያሳዩ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትም በተመሳሳይ ከባሕረ ሰላጤው መንግሥታት ጋር በኢኮኖሚ፣ በኢንቨስትመንት እና በደህንነት ጉዳዮች የተጣጣመ ፍላጎት ስላላቸው ፊታቸውን ወደ ቀጣናው እያዞሩ እንደሆነ አብራርተዋል።
የአፍሪካ ቀንድ እና የባሕረ ሰላጤው ቀጣና የጋራ የደህንነት ስጋት እንደተጋረጠባቸውም ነው ባለሙያው የጠቆሙት።
"ስለ የባሕር ላይ ውንብድና ካወራን ይሄ ለአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም ለባሕረ ሰላጤው ሀገራት የጋራ ስጋት ነው። ስለዚህም የጋራ ስጋቶች ሲኖሩ የሁለቱንም፤ የአፍሪካ ቀንድ እና የባሕር ሰላጤ ሀገራት፤ ቅንጅት እና ትብብር ይፈልጋል" ሲሉ ደምደመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X