ዓለም ለአፍሪካ ያለውን አተያይ በራሳችን ትርክት መቀየር አለብን ሲሉ ኢትዮጵያዊው የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዓለም ለአፍሪካ ያለውን አተያይ በራሳችን ትርክት መቀየር አለብን ሲሉ ኢትዮጵያዊው የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ተናገሩ
ዓለም ለአፍሪካ ያለውን አተያይ በራሳችን ትርክት መቀየር አለብን ሲሉ ኢትዮጵያዊው የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.05.2025
ሰብስክራይብ

ዓለም ለአፍሪካ ያለውን አተያይ በራሳችን ትርክት መቀየር አለብን ሲሉ ኢትዮጵያዊው የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ተናገሩ

በነገው እለት ተከብሮ የሚውለውን "የአፍሪካ ቀን" አስመልክቶ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቆይታ ያደረጉት ዝምድና አበበ የምዕራቡ ዓለም ሚዲያዎች አፍሪካን በአሉታዊ መንገድ የሚስሉበት መንገድ መቀየር አለበት ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

"ለወጣቱ ያለኝ መልዕክት የዲጂታል መድረኮችን ባሕላችንን ለማሳደግ፣ የጋራ ውይይት ለማድረግ፣  የአፍሪካ የጋራ ቅርስ ምን ማለት እንደሆነ ለመግለጽ በአዎንታዊ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲያውሉ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ዝምድና አክለውም የአፍሪካ ባሕላዊ እሴቶች ከተሸረሸሩባቸው መካከል መስኮች የትምህርት ስርዓቱ አንዱ ነው ብለዋል።

"የአፍሪካን የትምህርት ስርዓት ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለማድረግ የወጣቶች ግንባር ቀደም ተሳትፎ እና በባሕላቸው መኩራት እንዲሁም የባሕል ኢምፔሪያሊዝምን መቋቋም ወሳኝ ነው" በማለት የአፍሪካ ወጣቶች ሊጫወቱት ስለሚገባው ሚና አስረድተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0