የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ለብዙ የአፍሪካ ሀገራት መነሳሳትን ፈጥሯል ተባለ
16:02 24.05.2025 (የተሻሻለ: 16:24 24.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ለብዙ የአፍሪካ ሀገራት መነሳሳትን ፈጥሯል ተባለ
ለአራት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው አይ ዲ ፎር አፍሪካ ዓመታዊ ጉባኤ ተጠናቋል።
በጉባኤው ኢትዮጵያ ከተሳታፊ ሀገራት ከፍተኛ ልምድ ያገኘችበት እንደሆነ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሔ አርአያሥላሴ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ሀገር በቀል ዕውቀትን ተጠቅማ ያለማችው የዲጂታል መታወቂያ ቴክኖሎጂ አድናቆት እንደተቸረውና በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን ልምድ ለመካፈል ፍላጎት እንዳሳዩ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X