ኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ እያደጉ ያሉ ሀገራት በዓለም አቀፍ መድረክ ተሰሚነታቸው እንዲጨምር ለማረጋገጥ በትብብር ሊሠሩ ይገባል ስትል ጃካርታ ገለፀች
15:12 24.05.2025 (የተሻሻለ: 15:34 24.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ እያደጉ ያሉ ሀገራት በዓለም አቀፍ መድረክ ተሰሚነታቸው እንዲጨምር ለማረጋገጥ በትብብር ሊሠሩ ይገባል ስትል ጃካርታ ገለፀች
ለዚህም ሁለቱ ሀገራት በብሪክስ ማዕቀፍ በይበልጥ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ የኢንዶኔዥያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱጊኦኖ ጥሪ አቅርበዋል።
በሌላ በኩል የኢንዶኔዥያ-ኢትዮጵያ የንግድ ልውውጥ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረም ገልፀዋል።
የሁለቱ ሀገራት ንግድ በ2024 98 ሚሊየን እንደደረሠ እና ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 55 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ጠቁመዋል።
በኢንዶኔዥያ ከኢትዮጵያ አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ጋር ባደረጉት ውይይት ጃካርታ በግብርና እና ፋርማሱቲካል ዘርፍ በኢትዮጵያ ገበያ በስፋት መንቀሳቀስ ፍላጎት አላት ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X