ሱዳን የአሜሪካን የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅመሻል ክስ በፅኑ አስተባበለች
11:40 24.05.2025 (የተሻሻለ: 12:04 24.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሱዳን የአሜሪካን የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅመሻል ክስ በፅኑ አስተባበለች
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀገሪቱ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅማለች በሚል ውንጀላ ዩናይትድ ስቴትስ በሚቀጥለው ወር እጥላለው ያለችውን ማዕቀብ አውግዟል።
ሚኒስቴሩ በአሜሪካ አካሄድ መገረሙን እንደሚከተለው ገልጿል፦
🟠 ክሶቹ በመጀመሪያ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ጥቆማ ከወራት በፊት በመገናኛ ብዙኃን ወጥቷል።
🟠 አሜሪካ ጉዳዩን ሁለቱም ሀገራት አባል በሆኑበትና ሱዳን በሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት አባል ሆና በምትገኝበት የኬሚካል ጦር መሳሪያዎች ክልከላ ድርጅት አላቀረበችም።
ሱዳን ለስምምነቱ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች። በተጨማሪም ስምምነቱን የሚጥሱ ማናቸውንም የአንድ ወገን እርምጃዎች፤ በተለይም በሐሰተኛ ክስ የሌሎች መንግሥታትን ሉዓላዊነት እና ደህንነት የመሸርሸር ታሪክ ካላቸው አካላት የሚመጡትን ወድቅ እንደምታደርግ ገልጻለች።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X