ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር በሳይንስ እና ምርምር ዘርፍ መተባበር ትፈልጋለች ሲሉ የሩሲያ ባለሥልጣን ተናገሩ
10:23 24.05.2025 (የተሻሻለ: 10:44 24.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር በሳይንስ እና ምርምር ዘርፍ መተባበር ትፈልጋለች ሲሉ የሩሲያ ባለሥልጣን ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር በሳይንስ እና ምርምር ዘርፍ መተባበር ትፈልጋለች ሲሉ የሩሲያ ባለሥልጣን ተናገሩ
የሩሲያ ፌደሬሽን የሰብዓዊ ተቋም ኃላፊ ኢቭጌኒ ፕሪማኮቭ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በጣም የተቀራረቡ ሀገራት ናቸው ይላሉ።
"ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር ናት። ብዙ የዓለም ቅርስ የሆኑ ባህሎች አሏት። በሐይማኖት በጣም የተቀራረብን ነን። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን እና የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ቅርብ ግኑኝነት አላቸው" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።
ፕሪማኮቭ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በታሪክ እንዲሁም በሥነ-ፅሁፍ ጥብቅ የሆነ ቁርኝት አላቸውም ብለዋል።
ቅድመ አያቱ ኢትዮጵያዊ ናቸው ስለሚባሉት ታላቁ የሩሲያ ገጣሚ አሌክሳንደር ፑሽኪን እና በተለያዩ ጌዜያት በኢትዮጵያ በመምጣት ጥናት ስላደረገውና ስለ ኢትዮጵያ ብዙ የጻፈውን ኒኮላ ጉሚሉቭን በንግግራቸው አንስተዋል።
በአዲስ አበባ ለአሌክሳንደር ፑሽኪን እንዲሁም ለታላቁ ጠፈርተኛ ዩሪ ጋጋሪን መታሰቢያዎች እንዳሉ በመግለፅ ኒኮላ ጉሚሉቭ በተመሳሳይ መታሰቢያ እንዲኖረው እቅዶች እንዳሉ ጠቁመዋል
በተጨማሪም የሩሲያ የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የምርምር ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X