የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል ሲሉ ሚኒስትር ደኤታው ተናገሩ
17:09 23.05.2025 (የተሻሻለ: 17:24 23.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል ሲሉ ሚኒስትር ደኤታው ተናገሩ
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች ሚኒስትር ደኤታ ቀንአ ያደታ ሀገሪቱ በአፍሪካ ቀንድ የሚታዩ የጸጥታ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ቁልፍ እንደሆነች ገልፀው ሚናዋንም እየተወጣች ነው ብለዋል።
ባለሥልጣኑ ከሶስተኛው የአፍሪካ ቀንድ እና የኤደን ባሕረ ሰላጤ ውይይት ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የተናገሩት ነው።
አክለውም የኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል የሀገሪቱን ማንሰራራት የሚያመለክት እንደሆነ ተናግረዋል።
"የብሪክስ አባል መሆኗ እጅግ በጣም ወሳኝ ነው፡፡...ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታን ታገኛለች፡፡ ኢትዮጵያ ወደ ፊት እየተራመደች እንደሆነም ያሳያል፡፡ ባለፉት ሰባት ዓመታት ነው እንደዚህ ዓይነት ስኬታማ ለውጦችን እያሳያች የመጣችው" ሲሉ አብራርተዋል።
በሌላ በኩል የአፍሪካ ቀንድ እና የኤደን ባሕረ ሰላጤ ሀገራት ትብብር እና ቅንጅት ለቀጣናው ሰላም እና ደህንነት እንዲሁም ልማት አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X