270 ወታደራዊ አባላት እና 120 ሲቪሎች ወደ ሩሲያ ተመለሱ
16:51 23.05.2025 (የተሻሻለ: 17:04 23.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
270 ወታደራዊ አባላት እና 120 ሲቪሎች ወደ ሩሲያ ተመለሱ
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሩሲያ እና ዩክሬን በኢስታንቡል የደረሱት የእስርኞች ልውውጥ ስምምነት አካል እንደሆነ ገልጿል።
ሞስኮ እና ኪዬቭ ግንቦት 8 ቀን ከሶስት ዓመት በኋላ ባካሄዱት የመጀመሪያው ቀጥተኛ ድርድር 1 ሺህ እስረኞችን ለመለዋወጥ መስማማታቸው የሚታወስ ነው።
በእስረኞች ልውውጡ ዙሪያ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የሰጣቸው ቁልፍ መግለጫዎች፦
▪ ሩሲያ 270 የዩክሬን ጦር እስረኞችን እና 120 ሲቪሎችን አስተላልፋለች።
▪ በአሁኑ ወቅት የሩሲያ ወታደራዊ አባላቶች እና ሲቪሎች በቤላሩስ ይገኛሉ።
▪ በሩሲያ በኩል የተጀመረውን መጠነ ሰፊ የእስረኞች ልውውጥ በሚቀጥሉት ቀናት ለመቀጠል ታቅዷል።
▪ የሩሲያ ጦር አባላት እና ሲቪሎች ለሕክምና እና ለማገገም ወደ ሩሲያ ይጓጓዛሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X