"ኢትዮጵያ በኤደን ባሕረ ሰላጤ እና በቀይ ባሕር ቀጣና ሰላምና ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ በጣም ገንቢና አዎንታዊ ሚና መጫወት ትችላለች”

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"ኢትዮጵያ በኤደን ባሕረ ሰላጤ እና በቀይ ባሕር ቀጣና ሰላምና ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ በጣም ገንቢና አዎንታዊ ሚና መጫወት ትችላለች”
ኢትዮጵያ በኤደን ባሕረ ሰላጤ እና በቀይ ባሕር ቀጣና ሰላምና ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ በጣም ገንቢና አዎንታዊ ሚና መጫወት ትችላለች” - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.05.2025
ሰብስክራይብ

"ኢትዮጵያ በኤደን ባሕረ ሰላጤ እና በቀይ ባሕር ቀጣና ሰላምና ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ በጣም ገንቢና አዎንታዊ ሚና መጫወት ትችላለች”

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ ኢትዮጵያ ባላት ግዙፍ ኢኮኖሚ፣ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር እና የመሬት ስፋት ምክንያት ለቀጣናው የኢኮኖሚ ልማት ቁልፍ ሀገር ነች ሲሉ ከ3ኛው የቀይ ባሕር እና የኤደን ባሕረ ሰላጤ ውይይት ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"በአረብ ባሕረ ሰላጤ ሀገራት እና በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ ቀጣና ሰላምና ብልጽግናን ለማምጣት ብዙ የትብብር ዕድሎች አሉ" ብለዋል።

አያይዘውም የውይይቱ ዋና አላማ የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ በተመለከተ ያሉ ብዥታዎችን ለማጥራት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

"ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዲኖራት የምትፈልገው በዲፕሎማሲያዊ፣ በስምምነትና በሰላማዊ መንገዶች ብቻ ነው፡፡...በቀይ ባሕር የትኞቹም የጸጥታ እና የልማት እንዲሁም የኢኮኖሚ ጉዳዮች የኢትዮጵያን ፍላጎቶች ከግምት ውስጥ ያስገቡ መሆን አለባቸው፡፡”

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0