አሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የኃይል ቋት የመጀመሪያውን ኃይል ማቅረብ ጀመረ
13:55 23.05.2025 (የተሻሻለ: 14:04 23.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የኃይል ቋት የመጀመሪያውን ኃይል ማቅረብ ጀመረ
ፕሮጀክቱ በሦስት ተርባይኖች 100 ሜጋ ዋት የንፋስ ኃይል ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በታህሳስ 2018፣ 29 ተርባይኖች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገቡ በየዓመቱ ከ300 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ንጹህና ዘላቂ ኃይል ያመነጫል ተብሏል።
ይህም ከ140 ሺህ በላይ አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት በቂ ነው ሲል የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ፕሮጀክቱ ታዳሽ ኃይልን ወደ ግሪድ በማስገባት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እንደሚያስችል ተነግሯል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X