የዓለም የንግድ ድርጅት የግልግል ሥርዓት በአግባቡ እየሠራ አይደለም ሲሉ የሕግ ባለሙያው ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዓለም የንግድ ድርጅት የግልግል ሥርዓት በአግባቡ እየሠራ አይደለም ሲሉ የሕግ ባለሙያው ተናገሩ
የዓለም የንግድ ድርጅት የግልግል ሥርዓት በአግባቡ እየሠራ አይደለም ሲሉ የሕግ ባለሙያው ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.05.2025
ሰብስክራይብ

የዓለም የንግድ ድርጅት የግልግል ሥርዓት በአግባቡ እየሠራ አይደለም ሲሉ የሕግ ባለሙያው ተናገሩ

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዓለም አቀፍ የሕግ ጉዳዮች ዳይሬክተር ኑርልኝ ኢድርስ ድርጅቱ በሀገራት መካከል ለሚፈጠሩ ችግሮች ያስቀመጠው መፍትሔ በተግባር የሚፈፀም ባለመሆኑ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው ጠቁመዋል።

ከ11ኛው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ዓለም አቀፍ የሕግ ጉባኤ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ ኑርልኝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕግ የማውጣት ሂደት ውስጥ መሳተፍ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።

"አብዛኛውን ጊዜ በተለይም የዓለም የንግድ ድርጅት ስምምነት በሚረቀቅበት ጊዜ የአፍሪካ ሀገራት ፍላጎት በአግባቡ አይካተተም፤ ነገር ግን ከጊዜ በኋላ በተለይም ከዘላቂ ልማት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ማካተት አስፈልጓል። እያደጉ ያሉ እና የደሃ ሀገራትን ስጋት እና ፍላጎቶችን ከመፍታት አኳያ አሁንም ድረስ ተግዳሮቶች አሉ" ብለዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0