በዩኔስኮ የተመዘገቡት የኮንሶ አምባ መንደሮች ቅርስነታቸውን የመልቀቅ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለ
11:14 23.05.2025 (የተሻሻለ: 11:34 23.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበዩኔስኮ የተመዘገቡት የኮንሶ አምባ መንደሮች ቅርስነታቸውን የመልቀቅ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በዩኔስኮ የተመዘገቡት የኮንሶ አምባ መንደሮች ቅርስነታቸውን የመልቀቅ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለ
በአምባ መንደሮቹ የሚገኙ ጎጆ ቤቶችን ቆርቆሮ በማልበስ ቅርስነታቸውን እንዲለቁ እየተደረገ ነው ተብሏል።
አሁን ላይ 50 በመቶ የሚሆኑት ቆርቆሮ ለብሰዋል መባሉን የአካባቢውን የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
የአካባቢው ማሕበረሰብ ለጣሪያ ክዳን የሚጠቀምበትን የሳር ግብዐት ለማቅረብ እንቅስቃሴዎች በሚመለከታቸው አካላት መጀመሩም ነው የተጠቀሰው።
እ.አ.አ በ2011 በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የኮንሶ መልክዓ ምድር በካብ የታጠሩ መንደሮች፣ ባህላዊ ጎጆዎች፣ ጥብቅ ደኖች፣ ሐውልቶች እና ኩሬዎችን ይዟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X