በግለሰቦች እጅ የሚገኙ ቅርሶችን ማስመለስ ፈታኝ መሆኑን የቅርስ ማስመለስ ባለሙያው ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበግለሰቦች እጅ የሚገኙ ቅርሶችን ማስመለስ ፈታኝ መሆኑን የቅርስ ማስመለስ ባለሙያው ተናገሩ
በግለሰቦች እጅ የሚገኙ ቅርሶችን ማስመለስ ፈታኝ መሆኑን የቅርስ ማስመለስ ባለሙያው ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.05.2025
ሰብስክራይብ

በግለሰቦች እጅ የሚገኙ ቅርሶችን ማስመለስ ፈታኝ መሆኑን የቅርስ ማስመለስ ባለሙያው ተናገሩ

በፋሽስት ጣልያን ጦርነት ወቅት ከራስ ደስታ ዳምጠው አስከሬን ላይ የተወሰደው የወርቅ ሜዳሊያ በግለሰቦች አማካኝነት ለጨረታ መቅረቡን እንደ ማሳያ ያነሱት የኢትዮጵያ ቅርስ ባላ አደራ ማሕበር ምክትል ሰብሳቢ አሉላ ፓንክረስት ናቸው።

"የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ጨረታውን ለሚያካሂደው ድርጅት በፃፈው ደብዳቤ የተሰረቀን ቅርስ ማጫረት ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀሱ ድርጅቱ ጨረታውን ቢሰርዘውም ቅርሱን የያዘው ግለሰብ ተሰውሯል" ሲሉ የችግሩን አሳሳቢነት ያስረዳሉ።

ከሁለተኛው የቅርስ ጥናትና ምርምር ጉባኤ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቆይታ ያደረጉት አሉላ ፓንክረስት ቅርሶችን የማስመለስ እንቅስቃሴዎች ባላፉት ጥቂት ዓመታት እጅግ ተጠናክረው መቀጠላቸውን አፅንኦት ሰጥተዋል።

"የግለሰብ ቅርስ ሰብሳቢዎች ዓላማቸው ንግድ ስለሆነ ቅርሶቹ ትርጉም አይሰጧቸውም። በአንፃሩ እነዚህ ቅርሶች የኢትዮጵያ ባህላዊ ቅርስ አንድ አካል ናቸው። ወጣቱ ትውልድ ሊያያቸው ይገባል" ብለዋል።

ጨረታዎች ሲሰረዙ ሻጩ ግለሰብ ክፍያ እንደሚፈልግ በመግለፅ ቅርሶቹን በገንዘብ ከፍሎ ለማስመለስ ፈንድ መቋቋም አለበት ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0