“የአፍሪካ የልማት አጀንዳ ለውጭው ዓለም ማስተላለፍ እንደማይቻል ለመረዳት ከ50 ዓመታት በላይ ፈጅቶብናል” ኢትዮጵያዊው የግብርና ተመራማሪ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ“የአፍሪካ የልማት አጀንዳ ለውጭው ዓለም ማስተላለፍ እንደማይቻል ለመረዳት ከ50 ዓመታት በላይ ፈጅቶብናል” ኢትዮጵያዊው የግብርና ተመራማሪ
“የአፍሪካ የልማት አጀንዳ ለውጭው ዓለም ማስተላለፍ እንደማይቻል ለመረዳት ከ50 ዓመታት በላይ ፈጅቶብናል” ኢትዮጵያዊው የግብርና ተመራማሪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.05.2025
ሰብስክራይብ

“የአፍሪካ የልማት አጀንዳ ለውጭው ዓለም ማስተላለፍ እንደማይቻል ለመረዳት ከ50 ዓመታት በላይ ፈጅቶብናል” ኢትዮጵያዊው የግብርና ተመራማሪ

ተመራማሪው ፀደቀ አባተ የዓለም ‘የብዝሀ ሕይወት’ ቀንን አስመልከቶ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የኢትዮጵያ የሕዝብ ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መሄዱን አስረድተው ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የብዝሃ ሕይወት መዛባት ለመቀነስ ከዘመናዊ የግብርና ስርዓት ጋር አብሮ የሚሄድበት መንገድ መታሰብ አለበት ብለዋል።

"ሀገር በቀል እውቀቶች ለሁሉም የአፍሪካ ግብርና መሠረቶች ናቸው” ያሉት ተመራማሪው፤ በማሳያነት የኢትዮጵያን የእንሰት ተክልና የምዕራብ አፍሪካን የባምባራ ባቄላ ባህላዊ የግብርና ሰርዓት በመጥቀስ ትኩረት ተስጥቶ ሊሠራባቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የብዝሃ ሕይወትን በመጠበቅ ረገድ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በጋራ ያቋቋሙት የባዮሉጂካል ምርምር ማዕከል ወቅታዊ እና አስፈላጊ እንደሆነ አምናለሁ ሲሉ ባለሙያው አፅንኦት ሰጥተዋል።

"ይህ ትብብር በተለየ መንገድ ውጤታማ ሥራዎችን ያከናውናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ ባለፉት 50 በላይ ዓመታት ከሩሲያ ግብርና ብዙ ተሞክሮዎች ቀስመዋል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ዓለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ቀን ከግንቦት 12 እስከ 16 ድረስ “ከተፈጥሮ ጋር መስማማት ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከበረ ይገኛል፡፡

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0