ሩሲያ ለቡርኪናፋሶና ኒጀር ነፃ የሰብዓዊ ድጋፍ ልትሠጥ ነው
14:28 22.05.2025 (የተሻሻለ: 14:44 22.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ ለቡርኪናፋሶና ኒጀር ነፃ የሰብዓዊ ድጋፍ ልትሠጥ ነው
በእርዳታው የሚካተተው፦
🫛 ባለንበት የግንቦት ወር ቡርኪናፋሶ የሚደርሰው 709 ነጥብ 5 ቶን አተር እና
ኒጀር የምትረከበው 20 ሺህ ቶን ስንዴ ነው።
በቅርብ ጊዜ ሩሲያ የለገሰችው ሰብዓዊ እርዳታ የሚከተሉትንም ያካትታል፦
ለማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ 29 ሺህ 400 ቶን የናፍታ ነዳጅ እና
ለዚምባብዌ 559 ቶን አተር እና 164 ቶን የሱፍ አበባ ዘይት።
ሩሲያ ተጨማሪ የሰብዓዊ አቅርቦቶችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን እና በቂ የሆነ የምርት ክምችት እንዳለ የግብርና ሚኒስትር ኦክሳና ሉት ተናግረዋል።
መረጃው ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X