በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ የቀድሞውን በጥሬ ገንዘብ የሚደረግ ግብይት በልጧል ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ የቀድሞውን በጥሬ ገንዘብ የሚደረግ ግብይት በልጧል ተባለ
በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ የቀድሞውን በጥሬ ገንዘብ የሚደረግ ግብይት በልጧል ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.05.2025
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ የቀድሞውን በጥሬ ገንዘብ የሚደረግ ግብይት በልጧል ተባለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲጂታል ክፍያ ሥርዓት የሆነው ኢትስዊች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ይለብስ አዲስ ከኢትዮ ፋይናንስ ፎረም ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ የፊንቲክ ዘርፍ በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ ከፍተኛ እድገት ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

"የቅርብ ግዜ መረጃዎችን ከተመለከትን በሀገሪቱ የተካሄደው የዲጂታል ገንዘብ ልውውጥ በጥሬ ገንዘብ የሚደረገውን የገንዘብ ግብይት በጣም በልጧል" ብለዋል።

አክለውም ሀገሪቱ እየተከተለች ያለችውን የተዋሃደ ወጥ የክፍያ ስርዓት የማሳደግ እቅድ እንዳላት አብራርተዋል።

"ይህንን ስርዓት ድንበር ተሻጋሪ እንዲሁም ቀጣናውን እንዲያካትት የማድረግ እቅድ አለ፡፡ በአሁኑ ሰዓት የሁለትዮሽ ፈጣን እና የካርድ ክፍያን ለማዋሃድ ከተለያዩ ሀገራት ጋር እየሠራን ነው፡፡ ከአፍሪካ፣ እስያ እና አውሮፓ ሀገራት ጋር እየሠራን ነው” ብለዋል፡፡

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0