የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ 1 ሺህ 176 የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያዎች ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ 1 ሺህ 176 የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያዎች ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ 1 ሺህ 176 የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያዎች ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.05.2025
ሰብስክራይብ

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ 1 ሺህ 176 የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያዎች ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ

ከሚኒስቴሩ የተገኙ ተጨማሪ መረጃዎች፦

አሁን ላይ በአዲስ አበባ ከ90 በላይ የኤሌትሪክ ኃይል መሙያ ጣቢያዎች አሉ፡፡

ከከተማዋ ሁለተኛ ምዕራፍ የኮሪደር ማስፋፊያ ጋር ተያይዞ 54 ተጨማሪ የኤሌትሪክ ኃይል መሙያዎች በመገንባት ላይ ናቸው፡፡

ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋን ጨምሮ ቁልፍ በሆኑ የክልል ማዕከላት የኃይል መሙያ ጣቢያዎችም እየተገነቡ ነው፡፡

በዘርፉ የተደረጉ የአዋጭነት ጥናቶች በኢትዮጵያ ያለውን ፍላጎት ለሟሟላት በ50 ኪ.ሜ ርቀት አንድ የኤሌትሪክ ኃይል መሙያ በአጠቃላይ 1 ሺህ 50 ጣቢያዎችን መትከል እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል ሲል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

ኢትዮጵያ በመጪዎቹ አስር ዓመታት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎቿን ቁጥር 500 ሺህ ለማድረስ አቅዳለች።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0