የኢትዮጵያ እና ሩሲያ ወታደራዊ ትብብር ለሁለቱ ሀገራት የቆየ እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምሶሶ ነው ተባለ
19:36 21.05.2025 (የተሻሻለ: 12:14 22.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ እና ሩሲያ ወታደራዊ ትብብር ለሁለቱ ሀገራት የቆየ እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምሶሶ ነው ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ እና ሩሲያ ወታደራዊ ትብብር ለሁለቱ ሀገራት የቆየ እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምሶሶ ነው ተባለ
14ኛው የኢትዮጵያ-ሩሲያ ወታደራዊና ቴክኒካዊ ትብብር የበይነ መንግሥታት የሥራ ቡድን ስብሰባ ዛሬ በሞስኮ ተካሂዷል።
በዚህ ወቅት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታና የሥራ ቡድኑ ተባባሪ ሊቀመንበር ማርታ ሉዊጂ ስብሰባው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር ለመገምገም ጥሩ መድረክ ነው ብለዋል።
በአቅም ግንባታ ተነሳሽነቶችና በቴክኖሎጂ ሽግግር አማካኝነት የኢትዮጵያን የመከላከያ አቅም ለማሳደግም እንደሚረዳ ተናግረዋል።
የሩሲያ የሥራ ቡድን ሊቀመንበር አናቶሊ ፑንቹክ በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊና ቴክኒካዊ ትብብር የበለጠ ለማሳደግ ሩሲያ ዝግጁ እንደሆነች ገልጸዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
