"በታሪካዊው እና ታዋቂው ቦልሾይ ቴአትር ሽልማት ሲበረከትልኝ እጅጉን ኮርቼያለሁ"

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"በታሪካዊው እና ታዋቂው ቦልሾይ ቴአትር ሽልማት ሲበረከትልኝ እጅጉን ኮርቼያለሁ"
በታሪካዊው እና ታዋቂው ቦልሾይ ቴአትር ሽልማት ሲበረከትልኝ እጅጉን ኮርቼያለሁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.05.2025
ሰብስክራይብ

"በታሪካዊው እና ታዋቂው ቦልሾይ ቴአትር ሽልማት ሲበረከትልኝ እጅጉን ኮርቼያለሁ"

ዝነኛው የረቂቅ ሙዚቃ ፒያኖ ተጫዋች ግርማ ይፍራሸዋ በሩሲያ መዲና ሞስኮ በቅርቡ ተካሂዶ በነበረው “ብራቮ አዋርድ” በክላሲካል ሙዚቃ ዘርፍ ሽልማት ማግኘቱ የሚታወስ ነው።

በሽልማቱ ዙሪያ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ሩሲያ ውስጥ እውቅና ያገኛል ብሎ እንዳልጠበቀ ገልጿል።

"በሩሲያ ባሕል ውስጥ በዚህ ደረጃ ክብር አገኛለሁ ብዬ አልጠበኩም። በሩሲያ ባሕል ትልቅ ቦታ ባለው ቦልሾይ የኮንሰርት አዳራሽ ሽልማቱ ስለተበረከተልኝ እጅጉን ኩራት ተሰምቶኛል። ይህ ለኔ ሙዚቃ ዓለምን እንደሚያዳርስ ማረጋገጫ ነው። በሩሲያውያን ታዳሚያን እይታ ውስጥ ነኝ ብዬ አላሰብኩም" ብሏል።

ግርማ ይፍራሸዋ የመጀመሪያ የፒያኖ አስተማሪው ሩሲያዊ እንደነበሩ በማስታወስ ሩሲያ በተለይም በትምህርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ ብዙ እድሎችን እንደሰጠች ነግሮናል።

"በ70ዎቹ እና 80ዎቹ ሩሲያ ለኢትዮጵያ ብዙ የትምህርት እድሎችን ትሰጥ ነበር። ብዙ የማውቃቸው ጓደኞቼ እዛ ሄደው ሙዚቃ እና የተለያዩ የትምህርት ዓይነቶችን አጥንተዋል። ስለዚህ ግኑኝነቱ በጣም ጠንካራ እና ጥልቅ ነው"

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"በታሪካዊው እና ታዋቂው ቦልሾይ ቴአትር ሽልማት ሲበረከትልኝ እጅጉን ኮርቼያለሁ"
በታሪካዊው እና ታዋቂው ቦልሾይ ቴአትር ሽልማት ሲበረከትልኝ እጅጉን ኮርቼያለሁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.05.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0