የቀድሞ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር በፈፀሙት የሙስና ተግባር አስር ዓመት ተፈረደባቸው
17:42 21.05.2025 (የተሻሻለ: 18:04 21.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየቀድሞ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር በፈፀሙት የሙስና ተግባር አስር ዓመት ተፈረደባቸው

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቀድሞ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር በፈፀሙት የሙስና ተግባር አስር ዓመት ተፈረደባቸው
ሕገ-መንግሥታዊው ፍርድ ቤት ኦገስቲን ማታታ ፖንዮ ላይ የሚከተሉትን ተጨማሪ ቅጣቶች ወስኖባቸዋል፦
▪ለአምስት ዓመታት ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲታገዱ፣
▪አስቸኳይ እስር፣
▪ካባከኑት ገንዘብ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ንብረት መወረስ።
ፖንዮ ሲቆጣጠሩት የነበረ "የወንጀል ድርጅት" ከሚገባው በላይ ክፍያ ይጠይቅ እንደነበር ፍርድ ቤቱ ገልጿል።
የመዘበሩት ገንዘብ፦
▪ለቡካንጋ-ሎንዞ የግብርና-ኢንዱስትሪ ፓርክ የታሰበ 156 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር እና
▪ከደቡብ አፍሪካዊ ዜጋ ክሪስቶ ግሮብለር ጋር በማጭበርበር የተዘዋወረ 89 ሚሊዮን ዶላር ናቸው።
ፖንዮ እ.ኤ.አ ከ2012 እስከ 2016 ድረስ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ ስር በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል። የኮንጎ ሴኔት በአሁኑ ወቅት ካቢላ ኤም23 አማፂያንን በመደገፍ የቀረበባቸውን ክስ በተመለከተ ያለመከሰስ መብታቸውን ለማንሳት ጉዳዩን እየተመለከተ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X