የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሱዳን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መሾሟን አወደሰ
16:39 21.05.2025 (የተሻሻለ: 16:54 21.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሱዳን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መሾሟን አወደሰ
ካሚል ኤልታየብ ኢድሪስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው በሱዳን ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ይደግፋል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ማሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገልጸዋል።
የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሰኞ ዕለት ኢድሪስን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል።
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማን ናቸው?
◾ በሥራቸው ዲፕሎማት እና የሕግ ባለሙያ ናቸው፣
◾ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አእምሮዓዊ ንብረት ድርጅት ውስጥ እ.ኤ.አ ከ1997 እስከ 2008 ዋና ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል፣
◾በሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ በተለያዩ የሥራ መደቦች አገልግለዋል፣
◾በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሱዳን ቋሚ ተልዕኮ ውስጥ አገልግለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X